ተፈጥሮዓዊ ሐይማኖት


11 Aug
11Aug

ኢስላም የሰዉ ልጅ ሁሉ ተፈጥሯዊ  ሃይማኖት ነው ። "የሰዉ ልጅም ወደዚህች ምድር ሲመጣ /ሲወለድ/ ሙስሊም ሆኖ ነው ። አይሁድ ፣ ክርስቲያን ፣ አሊያም እሣት አምላኪ እንዲሆን የሚያደርጉት ወላጆቹ ናቸው።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ።
ከኢስላም በፊት በዐረቢያው ምድር ከጣዖት አምልኮ ርቀው ‘ ላ ኢላሀ ኢለላህ ’ ( ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም) ይሉ የነበሩ፤ በተፈጥሯዊ ሃይማኖታቸው የረጉ ሦስት ሰዎች እንደነበሩ ይነገራል። እነርሱም ፦
1- ዘይድ ኢብን ዐምር ኢብን ኑፈይል
2- አቡዘር አል ጊፋሪይ እና
3- ሰልማን አል ፋሪሲይ ናቸው ። 

ኋላ ላይም ሁለቱ ሶሐቦች እስልምናን ተቀብለዋል። ዘይድ ግን ነብዩን ቢያገኛቸዉም በመልዕክተኛነት ሲላኩ አልደረሰባቸውም። ዘይድ በአንድ አላህ አማኝ ሆኖ ነው የሞተው ። በመሃይማን መካከል ያደገ የኖረ ቢሆንም አንድም  ቀን ለጣዖት አላረደም፤ አልሰገደም።
ስለ ታላቅነቱ ሲያወሱ
‘ ዘይድ ኢብን ዐምር ኢብን ኑፈይል ብቻዉን ህዝብ ሆኖ ይነሣል ።’ ብለዋል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም ።

( فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّم )

“ፊትህን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት አዙር ፡ በርሱም ላይ ፅና ። (ይህ) አላህ የሰዉ ልጆችን የፈጠረበት ተፈጥሯዊ መንገድ ነዉና…..” ( አር ሩም ፡ 30 )

Comments
* The email will not be published on the website.