ሁሌም ወደ አሏህ እንምለስ (ተውባ እናድርግ)


11 Aug
11Aug

በሀዲስ አል ቁድሲ እንደተቀመጠው አላህ እንዲህ ብሏል:-

‹‹ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈጽማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኋለሁ።››

የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሐዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ ብሏል አሉ:-

‹‹የአደም ልጅ ሆይ! እኔን እስከጠራሀኝ ና እኔን እስከለመንከኝ ጊዜ ድረስ የሰራሀውን ሁሉ ይቅር እልሀለሁ (እምርልሀለሁ) ግድ የለኝም፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጅልህ በዝቶ የሰማይ ላይ ደመና ያክል ቢደርስ እና ምሀረት ከጠየቅከኝ እምርሀለሁ፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን የሚሞላ ወንጀል ተሸክመህ ከኔ ጋር ብትገናኝ (ወደኔ ብትመጣ)ና በኔ ላይ ምንም ካላጋራህ ምድር በሚሞላ ምህረት እቀበለሀላሁ(እምርሀለሁ)›› ቲርሚዚ ዘግበውታል።

Comments
* The email will not be published on the website.