አጫጭር ጽሁፎች


“ወደ አላህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ። በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው።” (አን-ነህል 16፤125)

በሀዲስ አል ቁድሲ እንደተቀመጠው አላህ እንዲህ ብሏል:- ‹‹ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈጽማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኋለሁ።›› የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሐዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ ብሏል አሉ:- ‹‹የአደም ልጅ ሆይ! እኔን እስከጠራሀኝ ና እኔን እስከለመንከኝ ጊዜ ድረስ የሰራሀውን ሁሉ ይቅር እልሀለሁ (እምርልሀለሁ) ግድ የለኝም፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጅልህ በዝቶ የሰማይ ላይ ደመና ያክል ቢደርስ እና ምሀረት ከጠየቅከኝ እምርሀለሁ፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን የሚሞላ ወንጀል ተሸክመህ ከኔ ጋር ብትገናኝ (ወደኔ ብትመጣ)ና በኔ ላይ ምንም ካላጋራህ ምድር በሚሞላ ምህረት እቀበለሀላሁ(እምርሀለሁ)›› ቲርሚዚ ዘግበውታል።

ስነ ምግባር በእስልምና ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቶታል፡፡ የአላህ መልእክተኛ የተላኩበትን ዓይነተኛ ዓላማ፣ የዳዕዋቸውን ጉልህ ሚና እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፡-

ኢስላም የሰዉ ልጅ ሁሉ ተፈጥሯዊ ሃይማኖት ነው ። "የሰዉ ልጅም ወደዚህች ምድር ሲመጣ /ሲወለድ/ ሙስሊም ሆኖ ነው ። አይሁድ ፣ ክርስቲያን ፣ አሊያም እሣት አምላኪ እንዲሆን የሚያደርጉት ወላጆቹ ናቸው።" ብለዋል ...

ተውሒድ ታላላቅ ፍሬዎችና ትሩፋቶች አሉት፡፡ ከእነዚህ ፍሬዎችና ትሩፋቶች መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መጥቀስ እንወዳለን፡- 1- በተውሒድ መልካም ጸጋዎች ይገኛሉ፡፡ የዱንያና የአኼራ ጭንቀቶች ይወገዳሉ፡፡ 2- ተውሒድ የተሟላ ጸጥታና መመራትን ያጎናጽፋል፡፡