ወደ እኔ ድህረ ገጽ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያልኩኝ፣ በገጾቼ ላይ የተለያዩ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ይጠቅማሉ ብዬ የማስባቸውን ቪድዮዎች፣ፅሁፎች እንዲሁም የተለያዩ ፖስቶችን በአላህ ፍቃድ የምለቅ መሆኑን እያስታወቅኩኝ፤ እርስዎንም ይህን ድህረ ገፅ ለወዳጅ ዘመድዎ በብዙሀን መገናኛ ገጾቻችሁ ላይ ሼር በማድረግ የምንዳው ተካፋይ እንዲሆኑ እጋብዛለሁ።
“ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ።በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው።” (አን-ነህል 16፤125)
“ወደ አላህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ። በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው።” (አን-ነህል 16፤125)
በሀዲስ አል ቁድሲ እንደተቀመጠው አላህ እንዲህ ብሏል:- ‹‹ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈጽማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኋለሁ።›› የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሐዲሰል ቁድስ አላህ እንዲህ ብሏል አሉ:- ‹‹የአደም ልጅ ሆይ! እኔን እስከጠራሀኝ ና እኔን እስከለመንከኝ ጊዜ ድረስ የሰራሀውን ሁሉ ይቅር እልሀለሁ (እምርልሀለሁ) ግድ የለኝም፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጅልህ በዝቶ የሰማይ ላይ ደመና ያክል ቢደርስ እና ምሀረት ከጠየቅከኝ እምርሀለሁ፡፡ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን የሚሞላ ወንጀል ተሸክመህ ከኔ ጋር ብትገናኝ (ወደኔ ብትመጣ)ና በኔ ላይ ምንም ካላጋራህ ምድር በሚሞላ ምህረት እቀበለሀላሁ(እምርሀለሁ)›› ቲርሚዚ ዘግበውታል።